
አዲስ አበባ: ጥር 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዓለም አቀፍ ጉባኤው ”የምልክት ቋንቋን መጠቀም ለመፃዒው ዘመን መፃኢው ዘመንን ምልክት ቋንቋን በመጠቀም” በሚል መሪ መልዕክት ነው እየተካሄደ የሚገኘው። ኢትዮጵያ እያስተናገደችው ያለው ጉባኤ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመጀመሪያ መኾኑን ተመላክቷል። ጉባኤው ለተከታታይ ሦስት ቀናት ይቆያል ነው የተባለው። በዘርፉ ለሚከናወኑ ተግባራት ስኬታማነት እገዛ የሚያደርጉ ጠቃሚ የፖሊሲ ግብዓቶች፣ ጥናቶች እና ምክረ ሃሳቦች ይቀርቡበታል ተብሏል።
ጉባኤውን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከብሔራዊ መስማት ከተሳናቸው ማኅበር፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር መዘጋጀቱም ተጠቅሷል። በጉባኤው ላይ መልዕክት ያስተላፉት የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ.ር) ጉባኤው መዘጋጀቱ ከብዙ ሀገራት ጋር የልምድ ልውውጦችን በማድረግ እና በመናበብ የምልክት ቋንቋን ከፍ ለማድረግ ይረዳል ብለዋል።
ኢትዮጵያዊ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ መስማት የተሳናቸው መኾናቸውን የገለጹት የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ ሁሪያ አሊ ጉባኤው በኢትዮጵያ መካሄዱ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች ጠቀሜታው የጎላ መኾኑን ገልጸዋል። ጉባኤው በሚካሄድባቸው 3 ቀናት ተሳታፊ ከኾኑ ሀገራት ጋር የልምድ ልውውጦች እንደሚያካሂዱም አመላክተዋል።
በጉባዔው ከተለያዩ የዓለም ሀገራት እና ተቋማት በአካል፣ በበይነ መረብ ከ600 በላይ ተሳታፊዎች እየተሳተፋ ነው።
ዘጋቢ:- ራሄል ደምሰው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!