የደሴ ከተማ መጭውን የጥምቀት በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየሠራ መኾኑን አስታወቀ።

21

ደሴ: ጥር 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደሴ ከተማ አሥተዳደር ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ በጥምቀት በዓል አከባበር ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ከጸጥታ አካላት ጋር መክሯል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያ ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን እና ታሪካዊነቱን ጠብቆ እንዲከበር የከተማ አሥተዳደሩ የጸጥታ ኀይል የቅድመ ዝግጅት ተግባራት አጠናቅቆ ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል።

የደሴ ከተማ አሥተዳደር በዓሉን ያለምንም የጸጥታ ችግር ለማክበር የጸጥታ መዋቅሩ ዝግጁ መኾኑ በመድረኩ ተገልጿል። የከተማ አሥተዳደሩ ፖሊስ ከአጋር የጸጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት እና በትብብር በመሥራት በዓሉን ያለምንም የጸጥታ ችግር ለማክበር ዝግጅት ማድረጉን የከተማ አሥተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር አበባው አሻግሬ ተናግረዋል።

የጥምቀት በዓል የአደባባይ በዓል እንደመኾኑ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ሁነቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር በቂ ዝግጅት በማድረግ ወደ ሥራ መግባቱን የከተማዋ ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ሰይድ አሊ ገልጸዋል።

ከሁከት እና ብጥብጥ የሚገኝ ትርፍ እንደሌለ የከተማው ሕዝብ ተረድቶ እንደከዚህ ቀደሙ በዓለ ጥምቀቱ በሰላም እንዲከበር ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በጋራ እንዲሠራም ጥሪ ቀርቧል።

ዘጋቢ፦ ደምስ አረጋ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ መልእክት!
Next articleዓለም አቀፍ የምልክት ቋንቋ የምርምር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።