የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ መልእክት!

32

የተፋሰስ ልማታችንን በማስፋት የአፈር ሀብታችንን ለብልጽግናችን ለማዋል መረባረብ ይገባናል፡፡ ዛሬ የ2017 ዓ.ም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሀገራዊ ንቅናቄ መጀመሩን አብሥረናል፡፡

የተፈጥሮ ሀብት ልማት ግባችንን ለማሳካት በየዓመቱ ከ14 ሚልዮን በላይ ዜጎችን በማሳተፍ መጠነ ሰፊ የተፋሰስ ልማት ተግባራትን በማከናወን እመርታዊ ለውጥ መጥቷል።

የተቀናጀ የተፈጥሮ ሀብትና የተፋሰስ ልማትን በመተግበራችንም ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ የመገንባት ቁርጠኝነታችንን አሳይተናል።

በዚህም የተራቆቱ አካባቢዎች አገግመዋል፣ የአፈር መከላት ቀንሷል፤ የደን ሽፋናችን ወደ 23.6 በመቶ አድጓል።

አርሶ አደሩ የተፋሰስ ልማቶችን በመጠበቅና በባለቤትነት በመያዝ የንብ ማነብ፣ የእንስሳት ርባታ፣ የመስኖ ልማት እና የፍራፍሬ ልማትን በመተግበር ተጠቃሚ እንዲሆን ተደርጓል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘርፉ እስካሁን ያስመዘገበችው ስኬት በመንግሥት አመራር፣ በሞያተኞች በኅብረተሰቡና በልማት አጋሮቻችን ተሳትፎ የተገኘ ድምር ውጤት ነው፡፡

በዚህ ዓመት በ4 ነጥብ አንድ ሚልዮን ሄክታር መሬት ላይ የሚካሄደውን የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና የተፋሰስ ልማት በማሳካት፤ አፈራችንን ለብልጽግናችን ለማዋል ሁሉም አካላት በትጋት እንዲረባረብ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

Previous articleየአፄ ቴዎድሮስ የልደት በዓል እየተከበረ ነው።
Next articleየደሴ ከተማ መጭውን የጥምቀት በዓል ያለምንም የጸጥታ ችግር ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየሠራ መኾኑን አስታወቀ።