የአፄ ቴዎድሮስ የልደት በዓል እየተከበረ ነው።

40

ባሕር ዳር: ጥር 6/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የዳግማዊ የአፄ ቴዎድሮስ 206ኛ የልደት በዓል በተለያያዩ የኪነጥበብ ሥራዎች በጎንደር ከተማ እየተከበረ ነው። ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ዛሬም ድረስ በተለያዩ መጠሪያ ስሞች ይወሳሉ። አባ ታጠቅ የፈረሳቸው ስም ነው። በጀግንነታቸው መይሳው ካሳ፣ በዙፋናቸው ደግሞ አፄ ቴዎድሮስ በሚሉ ስሞች ይጠራሉ።

ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ለኢትዮጵያ አንድነት መጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ትልቅ መሪ እንደነበሩ ታሪካቸው ምስክር ነው። የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ለሀገር ሥልጣኔ ከፍተኛ ፍላጎት የነበራቸው አፄ ቴዎድሮስ ጋፋት ላይ መድፍ በማሠራት ነገን አርቆ ማሰብ የቻሉ መሪ እንደነበሩ ተናግረዋል።

በጠላት መማረክን የሚፀየፉት ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ መቅደላ በተባለ ስፍራ ለሀገር አንድነት ከጠላት ጋር እያደረጉት በነበረው ፍልሚያ ከመማረካቸው በፊት በያዙት ሽጉጥ ራሳቸውን በክብር ሰውተዋል።

የአፄ ቴዎድሮስ የልደት በዓል ሲከበር ሀገራዊ አንድነትን እና ኅብረ ብሔራዊነትን በማሰብ እንዲኾን ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አሳስበዋል።

ጎንደር ከተማዋን ለማዘመን እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የመንግሥት ትኩረት ማሳያ ናቸውም ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“እየተተገበረ የሚገኘው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ ነው “ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር)
Next articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ መልእክት!