
ባሕር ዳር: ጥር 6/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ሀገራዊ ምክክር ለወጣቶች ፋይዳው የጎላ ነው። ከእነዚህም መካከል፦
✍️ ወጣቶች በነገዋ ኢትዮጵያ ላይ ባለቤትነት ተሰምቷቸው ለፖሊሲ ግብዓት የሚኾኑ ጥያቄዎችን ብሎም ሃሳቦችን እንዲያነሱ ያስችላል፤
✍️ ወጣቶች በንግግር እና በምክክር የሃሳብ ልዩነቶችን የመፍታትን ባሕል አንዲያዳብሩ የማስቻል አቅም ይኖረዋል፤
✍️ በተለያየ ፈርጅ ውስጥ የሚመደቡ ወጣቶች በችግሮቻቸው ዙሪያ በመነጋገር ሰላማዊ በኾነ መልኩ ልዩነቶችን የመፍታትን ባሕል እንዲያዳብሩ መንገዱን ይፈጥርላቸዋል፤
✍️ የሀገራዊ ምክክር ውጤቶች እና ምክረ-ሃሳቦች ሲተገበሩ የሂደቱ ዋነኛ ተዋናይ በመኾን ከሂደቱ ተጠቃሚ የሚኾኑበትን እና ሂደቱን እንዲያግዙ ምቹ መደላድል ይፈጥርላቸዋል፤
✍️ ወጣቶች በሀገራቸው ጉዳይ ባለቤት እንደመኾናቸው ሃሳባቸው ጎልቶ እንዲሰማ ያስችላል የሚሉት ከብዙ በጥቂቱ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ምንጭ፦ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!