ከሰላም ማጽናት ጎን ለጎን ሕዝብ እና መንግሥት የጣለባቸውን ኀላፊነት በመልካም ሙያዊ ሥነ ምግባር ለመወጣት ዝግጁ መኾናቸውን የብልጽግና ፓርቲ አባላት ገለጹ።

23

ደብረ ማርቆስ: ጥር 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሁለተኛውን የቅድመ መደበኛ ጉባኤ አካሂዷል። ‘ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት ነው የፓርቲው ሁለተኛ ቅድመ መደበኛ ጉባኤ የተካሄደው።

የከተማ አሥተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መልካሙ ሽባባው ሕዝቡ የሚያነሳቸውን የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮች በመፍታት ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ እየተሠራ ስለመኾኑ ገልዋል።

የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ሥራዎች በተያዘላችው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁም ክትትል እየተደረገ ስለመኾኑ ተናግረዋል።

አባላቱ የአመለካከት እና የተግባር አንድነት እንዲኖራቸው በማድረግ ውስጣዊ አንድነትን ለመገንባት እየተሠራ ነው ያሉት አቶ መልካሙ አባላቱ የተገኘውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ እና የተጀመሩ የልማት ሥራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ የሚጠበቅባቸውን ኀላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የጉባኤው ተሳታፊዎች በፓርቲው የተከናወኑ መልካም ተግባራትን ለማስቀጠል እና ውስንነቶችን ለማስተካከል የሚያግዝ መኾኑንም ተናግረዋል።

ችግሮችን በውይይት እና በንግግር መፍታት እንደሚገባ የተናገሩት የጉባኤው ተሳታፊ አባላት ከሰላም ማጽናት ጎን ለጎን ሕዝብ እና መንግሥት የጣለባቸውን ኀላፊነት በመልካም ሙያዊ ሥነ ምግባር ለመወጣት ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል።

በጉባኤው የፓርቲው የሁለት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፓርት ቀረቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየገቢ ግብር አዋጁ ምን ይላል?
Next article“ሀገራዊ ምክክር ለወጣቶች”