ምክር ቤቱ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።

31

ባሕር ዳር: ጥር 6/2017 ዓ.ም (አሚኮ)6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ በስብሰባው የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ደሳለኝ ወዳጄ የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡

ባቀረቡት ሪፖርትም የንብረት ታክስ በከተሞች ነዋሪ በኾነው ሕዝብ መካከል ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል የሚያሰፍን በመኾኑ ረቂቅ አዋጁ እንደተዘጋጀ ገልጸዋል፡፡ የመንግሥት አገልግሎትን እና መገልገያ ቦታዎችን በተሻለ ጥራት ለማቅረብ እንዲሁም ለማደስ እና ቀጣይነት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የሚወጣውን የኢንቨስትመንት ወጪ በንብረት ዋጋ ማደግ ምክንያት በሚጣል ታክስ አማካኝነት መሰብሰብ የሚያስችል በመኾኑ አዋጁ ተዘጋጅቷ ብለዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ በፍጥነት እየጨመረ ያለውን የከተማ ነዋሪ ሕዝብ የአገልግሎት መገልገያ ቦታዎች ፍላጎትን በአግባቡ ለማሟላት የሚያስችል ገቢ ትርጉም ባለው ሁኔታ ለማመንጨት እንደሚረዳም ተጠቁሟል፡፡

ምክር ቤቱ በስብሰባው የ14ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃል ጉባዔውንም በሙሉ ድምፅ አጽድቋል። የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋል መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“እንግዶችን ለመቀበል ዝግጁ ነን” የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች
Next articleጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ 41ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች፦