የትምህርት እና ሥልጠና መሠረታዊ ድርጅት የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ቅድመ መደበኛ ጉባኤ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

40

ባሕር ዳር: ጥር 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ የትምህርት እና ሥልጠና መሠረታዊ ድርጅት የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ቅድመ መደበኛ ጉባኤ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። በቅድመ ጉባኤው ኮንፍረንስ ላይ የትምህርት እና ሥልጠና መሠረታዊ ድርጅት አመራሮች እና አባላት እየተሳተፉበት ይገኛሉ፡፡

በውይይቱ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ እና የኢንስፔክሽንና ሥነ ምግባር ኮሚሽን ሪፖርቶች ቀርበዋል።

ብልፅግና ፓርቲ በአንደኛ ጉባኤው ወቅት የፓርቲው የትኩረት አቅጣጫዎች እና ተግባራዊ አፈጻጸሙ በስፋት እና በጥልቀት የሚገመገምበት እንዲሁም የ2ኛው ጉባኤ እድሎች እና ተስፋዎች ላይ በሳል ውይይት እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የገበያ ማዕከላቱ የግብይት ሰንሰለቱን ያሳጥራሉ” ኢብራሒም ሙሐመድ (ዶ.ር)
Next article“5 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በሥነ ሕይወታዊ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ ይሸፈናል” ግብርና ሚኒስቴር