
ባሕር ዳር: ጥር 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በተያዘው በጀት ዓመት ስድስት ወራት ከሀገር ውስጥ ታክስ እና ከጉምሩክ ቀረጥ እና ታክስ 451 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር መሠብሠቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።
የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ እንደገለጹት በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት በሀገር ውስጥ ታክስ 247 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር መሠብሠብ ተችሏል።
በጉምሩክ በኩል ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ 203 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ተሠብስቧል ብለዋል።
የገቢ አሠባሠቡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ106 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ብልጫ ማሳየቱንም አስረድተዋል።
የኢዜአ ዘገባ እንደሚያመላክተው በመንግሥት የተወሰደው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃ ለውጤቱ እተዋጽኦ ሲሉ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ጠንካራ የክትትል ሥርዓት መዘርጋቱ እና መተግበሩ ለገቢ አሰባሰቡ ውጤታማነት አስተዋጽኦ ያበረከቱ ጉዳዮች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!