ከ284 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ ለመሥራት ማቀዱን የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

43

ፍኖተ ሰላም: ጥር 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ ተፋሰሶችን በማልማት የእርሻ መሬትን በጎርፍ እንዳይጋለጥ እና ለምነቱ እንዲጨምር ዓይነተኛ ሚና አለው። የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ የ2017 ዓ.ም የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ የማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ በፍኖተ ሰላም ከተማ ተካሂዷል።

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የተገኙት የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዓባይ ዓለሙ የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ የሕልውና ጉዳይ በመኾኑ ማኅበረሰቡ በንቅናቄ ሊሳተፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። በተያዘው በጀት ዓመት በ284 ሺህ 395 ሄክታር መሬት ላይ 526 ተፋሰስ የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ ለመሥራት መታቀዱን የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ ተስፋዬ አስማረ ገልጸዋል። ለተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ ሥራው የሚያስፈልጉ የልማት መሳሪያዎች ማሟላት እና ቀያሽ አርሶ አደሮችን ማሰልጠን መቻሉን ነው ኀላፊው የተናገሩት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሀገር ፍቅር ያለው ትውልድ መገንባት የብልጽግና ፓርቲ ዋና ዓላማ ነው።
Next article“ሀገርን እና ወገንን መውጋት ትርፉ ውርደት እንጂ ክብር ሊኾን አይችልም” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው