የሀገር ፍቅር ያለው ትውልድ መገንባት የብልጽግና ፓርቲ ዋና ዓላማ ነው።

48

ሁመራ: ጥር 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት “ከቃል እስከ ባሕል!” በሚል መሪ ሀሳብ ከጥር ሁለት እስከ አራት ሲያካሂድ የነበረውን ሁለተኛ ቅድመ መደበኛ ጉባኤ አጠናቅቋል።
ቅድመ መደበኛ ጉባኤው ፓርቲው ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ያስመዘገባቸውን ድሎች፣ ክፍተቶች እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን ገምግሟል።

የሀገረ መንግሥት ግንባታን እውን ለማድረግ “ገዢ ትርክታችን ብሔራዊነት እና አርበኝነት ነው” ያሉት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ እና የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አሸተ ደምለው ናቸው።
ዋና አሥተዳዳሪው አክለውም የሀገር ፍቅር ያለው ትውልድ መገንባት የብልጽግና ፓርቲ ዋና ዓላማ መኾኑን ተናግረዋል።

የቅድመ መደበኛ ጉባኤው ዋና ዓላማ ለመደበኛው ጉባኤ ስንቅ የሚኾኑ ግብዓቶችን መሰብሰብ መኾኑን በመጥቀስ ጉባኤው ያነሳቸው መሠረታዊ ጥያቄዎችም መፈታት እንዳለባቸው የዞኑ የብልጽግና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ገብረ እግዚአብሔር ደሴ ተናግረዋል።
ብልጽግና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ አዎንታዊ አስተዋጽኦ በማበርከት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እየሠራ መኾኑን ኀላፊው ገልጸዋል።

በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ዘርፎች ተጨባጭ ድል መመዝገቡን የዞኑ ማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ አብዱልዋስዕ አቡበከር ገልጸዋል።
አቶ አብዱልዋስዕ አክለውም ፓርቲው እነዚህን ድሎች ያሳካው በችግር ጊዜ ተወልዶ፣ ችግሮችንም አልፎ ነው ብለዋል።

ስኬቶቻችንን በማጉላት ማስቀጠል እና ክፍተቶቻችንን ለማስተካከል ገምግመናል ያሉት ደግሞ የዞኑ ማዕድን ኃብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ትዕግስት ጸጋዬ ናቸው።
ከተመዘገቡ ስኬቶች ባሻገር ትኩረት ተሰጥቶ ሊሠራበት ይገባል ብሎ ጉባኤው ያመነበት የአማራ ሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄዎች በአግባቡ እንዲፈቱ እየተሠራ መኾኑንም ኃላፊዋ አስገንዝበዋል።

በኮንፈረንሱ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አሸተ ደምለው፣ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ገብረ እግዚአብሔር ደሴን ጨምሮ የዞኑ መሪዎች እና የወረዳ አሥተባባሪ ኮሚቴ መሪዎች ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሀገር እና ሕዝብን የካደ ታሪክ የለውም” አቶ ደሳለኝ ጣሰው
Next articleከ284 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የተፈጥሮ ሃብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ ለመሥራት ማቀዱን የምዕራብ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።