
ባሕር ዳር: ጥር 4/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ከዩጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
ከአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ፕሮግራም (ካዳፕ) ልዩ ጉባኤ ጎንለጎን በተደረገው ውይይት ግብርናን ማዘመን፣ የዓባይ ውኃ በጋራ በፍትሃዊነት መጠቀም እና የአፍሪካ ኅብርትን ማጠናከር በሚያስችሉ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ውይይቱም ስኬታማ እንደነበርም ፕሬዚዳንት ታዬ በኤክስ ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ገልፀዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!