የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የሚሊሻ እና የሰላም አስከባሪ አባላትን እያስመረቀ ነው።

52

ባሕር ዳር: ጥር 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የሚሊሻ እና የሰላም አስከባሪ አባላትን እያስመረቀ ነው። ሥልጠናው የማጠናከሪያ እና ለአዲስ የሚሊሻ አባላት ሲሰጥ የቆዬ ነው።
በአማራ ክልል የተፈጠረውን የሰላም እጦት ለማስተካከል እና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የጸጥታ ኃይሎችን የማጠናከር ሥራ እየተሠራ ነው። በክልሉ ለሚሊሻ እና ለሰላም አስከባሪ ኃይሎችም ሥልጠና እየተሠጠ ነው።

የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደርም በከተማዋ ያለውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ነው የሚሊሻ እና የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን አሠልጥኖ እያስመረቀ የሚገኘው።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች አሥተባባሪ እና የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው፣ የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article✍️የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር!
Next article“የብልጽግና ፓርቲ በርካታ ፈተናዎች ቢገጥሙትም ችግሮችን በመመከት ድሎችን አስመዝግቧል” የምዕራብ ጎንደር ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት