በዋድላ ወረዳ የሰብል ቃጠሎ መድረሱ ተገለጸ፡፡

59

ወልድያ: ጥር 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም በዋድላ ወረዳ 03 ቀበሌ ሰብል መቃጠሉን የወረዳው ዋና አሥተዳዳሪ ሲልማ ባዬ አስታውቀዋል። ቃጠሎው የደረሰው ቀጭኔ ተብሎ በሚጠራው ጎጥ ላይ ሲኾን በቃጠሎው የ52 አርሶ አደሮች ሰብል መውደሙን ነው ያስረዱት።

የወረዳው ሰላም እና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኢንስፔክተር ሀብቴ በላይ ጉዳቱ በደረሰበት ወቅት በቦታው መገኘታቸውን ገልጸዋል። ጉዳቱ በክልሉ ካለው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ጋር የተዛመደ ሳይኾን በጥንቃቄ ጉድለት መከሰቱን ለአሚኮ ገልጸዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዓለሙ ይመር ጉዳቱ መድረሱን መረጃው እንዳላቸው ነግረውናል። የጉዳቱን መጠን እና የተጎጂ ወገኖችን ልየታ በማድረግ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ጽሕፈትቤታቸው ዝግጁ መኾኑን ነው ለአሚኮ ያስረዱት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለኢትዮጵያውያን እና መንግሥታቸው ያልተደረገ ድጋፍ እንደተደረገ አድርጎ ማውጣት ተገቢ እንዳልኾነ የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ተማላሾች አገልግሎት አስታወቀ፡፡
Next articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክት፦