
ባሕር ዳር: ጥር 2/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ የተከሰተው ሰደድ እሳት በሰው ሕይዎት እና በንብረት ላይ ባደረሰው ጉዳት የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ገልጻለች፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በደረሰው ጉዳት ኢትዮጵያ ማዘኗን አስታውቋል፡፡
በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ከአሜሪካ መንግሥት እንዲሁም በሎስ አንጀለስ አካባቢ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጎን መኾናቸውን አረጋግጧል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!