በሰሜን ወሎ ዞን ሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡

27

ወልድያ: ጥር 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ወሎ ዞን አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር ኮንፈረንሱ በየደረጃው ያለው የፓርቲ አመራር እና አባላት የሚገኝበትን ሁኔታ በጥልቀት ገምግመን በቀጣይ የፓርቲውን ተልዕኮ በአመለካከት የጠራ፣ በተግባር ውጤታማ የሆነ ቁርጠኛ መዋቅር ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በዚህ ጉባኤ በፓርቲያችን ጥረት ባለፉት ሁለት አመታት በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ በውስጠ ፓርቲ ሥራዎቻችን እና በሥነ ምግባር እና የቁጥጥር ጉዳዮች የተጎናጸፍናቸውን የድል ስኬቶች እና ያጋጠሙ ፈተናዎችን እንዲሁም ፈተናዎቹን ለመሻገር የሄድንባቸውን ርቀቶች ገምግመን አቅጣጫ እናስቀምጣለን ነው ያሉት።

በብልጽግና ፓርቲ የሰሜን ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ከድር ሙስጦፋ ጠንካራ ፓርቲ የመገንባት ትልማችንን በማጠናከር በፓርቲያችን መሪነት የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል፣ ድክመቶችን ለማረም እና ለቀጣይ ትግል ይበልጥ መዘጋጀት የጉባኤው ኮንፈረንስ መካሄድ ዋና ዓላማ መኾኑን አስረድተዋል፡፡

የጋራ ሀገራዊ ህልማችን እውን እንዲኾን እኩልነትን መቀበል፣ አብሮነትን ማጎልበት፣ ወንድማማችነትን ማጠናከር፣ አሰባሳቢ ትርክትን በንግግር እና በተግባር መኖር እንደሚያሥፈልግ ለጉባኤ ኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ኮንፈረንሱ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲኾን የዞን፣ የወረዳ እና ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ አመራሮች እና የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ነው፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ብልጽግና ፓርቲ የገባቸውን ቃሎች በመፈጸም ሀገራዊ እና ገዥ ትርክቶችን ማጽናት ላይ በትኩረት እየሠራ ነው” የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር
Next articleኢትዮጵያ በካሊፎርኒያ በደረሰው ሰደድ እሳት እና በተፈጠረው ጉዳት የተሰማትን ጥልቅ ሐዘን ገለጸች።