“ብልጽግና ፓርቲ የገባቸውን ቃሎች በመፈጸም ሀገራዊ እና ገዥ ትርክቶችን ማጽናት ላይ በትኩረት እየሠራ ነው” የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር

27

ከሚሴ: ጥር 02/2017 ዓ.ም(አሚኮ) “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ቃል በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ዙር ጉባዔ ቅድመ ጉባዔ በከሚሴ ከተማ መካሄድ ጀምሯል። የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ አሊ አባፋሮ ብልጽግና ፓርቲ በፈተናዎች የማይሸነፍ፣ የጠራ ሃሳብ የያዘ እና ሰው ተኮር ፓርቲ ነው ብለዋል። ባለፋት ዓመታት በተፈጠሩ ሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ ፈተናዎች ያልተበገረ፣ የሚጨበጥ ሁለንተናዊ ዕድገት ያስመዘገበ ፓርቲ እንደኾነም ገልጸዋል።

“ፓርቲው የገባቸውን ቃሎች በመፈጸም ሀገራዊ እና ገዥ ትርክቶችን ማጽናት ላይ በትኩረት እየሠራ ነው” ብለዋል። ኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን በማጎልበት ሀገረ መንግሥት እንዲፈጠር ዘርፋ ብዙ ሥራወችን እያከናወነ እንደሚገኝ እና ቃል የገባውን የመፈጸም ባሕልን ተግባራዊ እያደረገ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አሕመድ ሁሴን ብልጽግና ፓርቲ ለውጥ በማያመጡ ባሕሎች ተቸንክሮ የሚቆም ሳይኾን ሀገራችንን በሚመጥን አሻጋሪ ስኬታማ የለውጥ ባሕልን ማዕከል ያደረገ ፓርቲ እንደኾነ ገልጸዋል። በዚህም ዘርፋ ብዙ ስኬታማ ውጤቶችን አስመዝግበናል ነው ያሉት።

በመርሐ ግብሩ ላይ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ዋና አሥተዳዳሪ አሕመድ ዓሊ አባፋሮ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አሕመድ ሁሴንን ጨምሮ የዞን የሥራ ኀላፊዎች፣ የወረዳ እና የከተማ አሥተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አሥተባባሪዎች እንደተገኙ ከብሔረሰብ አሥተዳደሩ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ላይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየደሴ ከተማ አሥተዳደር ታላላቅ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ የመፈጸም አቅም ማደጉን በተግባር አሳይቷል።
Next articleበሰሜን ወሎ ዞን ሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡