የመሪዎችን ዓቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ ነው።

17

እንጅባራ: ጥር 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት ሁለተኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ ቅድመ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው። የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዓለሙ ሰውነት ብልጽግና አውዳሚ የፖለቲካ ባሕልን በማስቀረት አዲስ አካታች የፖለቲካ ሥርዓት ለመትከል እየተጋ ያለ ፓርቲ መኾኑን ተናግረዋል።

“የመሪዎችን አቅም ወደ ተቋም ግንባታ በማሳደግ የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል እና ድክመቶችን ለማረም እየተሠራ መኾኑንም” ኀላፊው ገልጸዋል። በጉባዔው ፓርቲው በምሥረታው ማግስት ባካሄደው 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች፣ የተገኙ ስኬቶች እና ያጋጠሙ ችግሮች በዝርዝር እንደሚገመገሙም አንስተዋል።

ጉባዔው የፓርቲውን ተልዕኮዎች ለማሳካት የሚያስችሉ ምስጉን እና ብቃት ያላቸው መሪዎችን አቅም ለመገንባት ያግዛልም ነው ነው ያሉት። የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ዋና አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው ብልጽግና ፓርቲ ከባለፈው ሥርዓት የተቀበላቸውን ወረቶች እንደ ምንዳ በመጠቀም እና እዳዎችን ደግሞ በአሸናፊነት እየተወጣ ያለ አካታች እና ኅብረ ብሔራዊ ፓርቲ መኾኑን ተናግረዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ስኬቶችን ለማስቀጠል እና ጉድለቶችን ለማረም የአመራሩን ቁርጠኝነት የሚያላብስ እንደኾነም ዋና አሥተዳዳሪው አንስተዋል። ለሁለት ቀናት በሚቆየው የቅድመ መደበኛ ጉባዔ ኮንፈረንስ ከወረዳ እና ከተማ አሥተዳደሮች የተውጣጡ የሥራ ኀላፊዎች እየተሳተፍ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበላሊበላ ሴት አስጎብኝዎች እንዲበራከቱ እየተሠራ ነው።
Next articleሰላምን ለማስፈን እና ልማትን ለማምጣት የነበረውን ጥንካሬ እና ድክመት መፈተሽ እንደሚያስፈልግ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ፡፡