“መንግሥት እና ማኅበረሰቡ ተግባብቶ በመሥራቱ በከተማዋ በርካታ ሰው ተኮር ተግባራት ተሠርተዋል” የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር

23

ደሴ: ጥር 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሁለተኛ ቅድመ መደበኛ ጉባኤ ኮንፈረንስ እያካሄደ ነው። የጉባኤው ተሳታፊዎች ፓርቲው ለኅብረተሰቡ የገባውን ቃል ምን ያህል ፈጽሟል የሚለው የሚገመገምበት መድረክ መኾኑን ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት ያልተመለሱ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያስችላቸውን ግንዛቤ የሚጨብጡበት ጉባኤ እንደሚኾንም አስረድተዋል። የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሙሉጌታ አቢ ጉባኤው ፓርቲው በሁለት ዓመት ተኩል ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለመዳሰስ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና ማኅበረሰቡ ተግባብቶ በመሥራቱ በከተማዋ በርካታ ሰው ተኮር ተግባራት መከናወናቸውንም ተናግረዋል። የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መሐመድ አሚን የሱፍ ፓርቲው ለሕዝቡ የገባውን ቃል ወደ ተግባር በመቀየር በሀገር እና በክልል ደረጃ ስኬቶች ተመዝግበዋል ነው ያሉት።

የመጡ ለውጦችንም ቀጣይነት ለማረጋገጥ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የተለወጠ የፓለቲካ ባሕል እሳቤን ማዳበር ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አስገንዝበዋል። ጉባኤው ለተከታታይ ሁለት ቀናት እንደሚካሄድም ለማወቅ ተችሏል።

ዘጋቢ፦አንተነህ ፀጋዬ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሀገር በቀል ስጦታዎች ምርት በላሊበላ!
Next articleበላሊበላ ሴት አስጎብኝዎች እንዲበራከቱ እየተሠራ ነው።