ድሎችን በማስፋት እና ስህተቶችን በማረም ሀገራዊ ለውጡ እንዲቀጥል እየተሠራ ነው።

22

ፍኖተ ሰላም: ጥር 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎጃም ዞን ”ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሀሳብ የከፍተኛ እና መካከለኛ መሪዎች ሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ ቅድመ መደበኛ ጉባኤ ኮንፈረንስ በፍኖተ ሰላም ከተማ እየተካሄደ ነው።

በኮንፈረንሱ ላይ ተገኝተው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አባይ አለሙ ፓርቲው ከተመሰረተ ጀምሮ በርካታ ችግሮች መፈጠራቸውን አንስተዋል። ለውጦችን እና ማሻሻያዎችን በማድረግ ብሔራዊ ትርክትን ለመፍጠር በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መኾናቸውን ገልጸዋል።

ኮንፈረንሱም በየደረጃው ያለ መሪ ጥንካሬዎችን እና ድክመቶችን ለመገምገም ያለመ መኾኑን አቶ አባይ ተናግረዋል።

የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ እድሜዓለም አንተነህ በፖለቲካ እና በኢኮኖሚ የተገኙ ድሎችን በማስፋት እና የተሠሩ ስህተቶችን በማረም ሀገራዊ ለውጡ እንዲቀጥል እየተሠራ ብለዋል።

በተለይ አመራሩ የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት እንዲፈጠር ተደርጓል ነው ያሉት። በኮንፈረንሱ ላይም የወረዳ እና የዞን መሪዎች እየተሳተፉ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበፓርቲው የቁጥጥር፣ ሥነ ምግባር እና በመተዳደሪያ ደንቡ የተሻሻሉ አንቀጾች ላይ ውይይት ይደረጋል።
Next articleበዋድላ የደረሰው ጉዳት ከጉዳትም በላይ ነው።