በፓርቲው የቁጥጥር፣ ሥነ ምግባር እና በመተዳደሪያ ደንቡ የተሻሻሉ አንቀጾች ላይ ውይይት ይደረጋል።

44

ባሕር ዳር: ጥር 02/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ”ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ ቅድመ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ኮንፈረንስ ማድረግ ጀምሯል።

በኮንፈረንሱ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና የከተማ አሥተዳደሩ ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሞላ ሁሴንን ጨምሮ የከተማ መሪዎች ተገኝተዋል።

ከቃል እስከ ባሕል፣ የአመራር ችግሮችን በመፍታት ራዕይን ማሳካት፣ የፓርቲው የቁጥጥር እና ሥነ ምግባር እንዲኹም በመተዳደሪያ ደንቡ የተሻሻሉ አንቀጾች ላይ መወያየት የኮንፈረንሱ ዋና ዋና አጀንዳዎች ናቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየቅዱስ ላሊበላ ዋናው ጥገና እንዲጀመር ተጠየቀ።
Next articleድሎችን በማስፋት እና ስህተቶችን በማረም ሀገራዊ ለውጡ እንዲቀጥል እየተሠራ ነው።