ብልጽግና ፓርቲ ፈተናዎችን እያለፈ የኅብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እየሠራ ያለ ፓርቲ ነው” የምሥራቅ ጎጃም ዞን

15

ደብረ ማርቆስ: ጥር 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት የምሥራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሁለተኛ ቅድመ መደበኛ ጉባኤ ኮንፈረንስ በደጀን ከተማ እየተካሄደ ነው። በጉባኤው የዞን እና የወረዳ የሥራ ኀላፊዎች እየተሳተፉ ነው።

በጉባኤው የምሥራቅ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋዬ በላይ ብልጽግና ፓርቲ ብዙ ፈተናዎችን እያለፈ የኅብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እየሠራ ነው ብለዋል። ጉባኤው ባለፉት ዓመታት ያጋጠሙ ችግሮችን በመገምገም ቀጣይ ለሚሠሯቸው ሥራዎች የሚጠቅም ሀሳብ የሚገኝበት ይኾናል የሚል ዕምነት እንዳላቸውም ነው አቶ ተስፋዬ የተናገሩት።

ጉባኤው ፓርቲው ባለፉት ሁለት ዓመታት የኅብረተሰቡን ችግር ለመፍታት የሠራቸው ሥራዎችን የሚገመግምበት እና የቀጣይ አቅጣጫዎች የሚያስቀምጠበት ነው ብለዋል። ፈተናን እንደ ጥንካሬ በመጠቀም በየአካቢው የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት በማድረግ የኅብረተሰቡን ችግር መፍታት ከመሪዎች እንደሚጠበቅም ነው አቶ ተስፋዬ ያስረዱት።

በጉባኤው የተገኙት የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ኑርልኝ ብርሃኑ ብልጽግና ፓርቲ በፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ፓርቲ ነው ብለዋል። ፓርቲው በቀጣይ የኅብረተሰቡን መሠረታዊ ችግሮች በመቅረፍ የተሻለች ሀገር ለትውልድ ለማስረከብ እየሠራ እንደሚገኝም ነው ዋና አሥተዳዳሪው የተናገሩት።

ፓርቲው በሀገሪቱ ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ውስብስብ ችግሮችን እያለፈ ያለ ፓርቲ ነው ያሉት አቶ ኑርልኝ የጉባኤው ተሳታፊዎች ከአሁን በፊት ከተከሰቱ ችግሮች ትምህርት በመውስድ በቀጣይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በቀላሉ ለመፍታት የሚያስችል ግብዓት የሚያገኙበት መድረክ መኾኑንም ተናግረዋል።

የጉባኤው ተሳታፊዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት ፓርቲው ለኅብረተሰቡ የገባውን ቃል ምን ያህል ፈጽሟል የሚለው የሚገመገምበት መድረክ በመኾኑ ባለፉት ዓመታት ያልተመለሱ የሕዝብ ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያስችላቸውን ግንዛቤ የሚያገኙበት እንደሚኾንም ተናግረዋል።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ መሪዎች ሃሳባቸውን በሰፊው በማንሳት የቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጡበት እንደሚኾንም ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleብልጽግና ችግሮች ቢገጥሙትም ከሕዝቡ ጋር በመሥራት በስኬት መወጣት ችሏል።
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ያስተላለፍት መልዕክት።