
ደሴ: ጥር 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ኮንፈረንስ ማካሄድ ጀምሯል። በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የደቡብ ወሎ ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ ዳኘው ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት በርካታ ችግሮች ቢገጥሙትም ከሕዝቡ ጋር በመሥራት ችግሮችን በስኬት መወጣት መቻሉን ተናግረዋል።
የመስኖ ስንዴ፣ የሌማት ቱሩፋት፣ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ ሌሎችም የሕዝቡን የመልማት ጥያቄ የሚመልሱ ሥራዎች መሠራታቸውን ገልጸዋል፡፡ አቶ ተስፋ ባለፉት ዓመታት የታዩ የሥራ አፈጻጸሞችን እና የተገኙ ስኬቶችን ለመገምገም እና በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዓላማ ያለው ጉባኤ መኾኑን ጠቁመዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮነን በፖለቲካ፣ በማኅበራዊ እና በኢኮኖሚው ዘርፍ አመርቂ ሥራዎች መሠራታቸውን እና የዞኑን ሰላም ከማረጋገጥ ባሻገር በርካታ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን መሥራት ተችሏል ብለዋል።
ጉባኤው ለተከታታይ ሁለት ቀናት እንደሚቆይ ታውቋል።
ዘጋቢ:- ሰልሀዲን ሰይድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!