
ደብረ ማርቆስ: ጥር 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ማርቆስ ከተማ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት የሁለተኛው ዙር የብልጽግና ፓርቲ ቅድመ መደበኛ ጉባዔ ተካሒዷል። በመድረኩ የሥራ ኀላፊዎች ያሉባቸውን ክፍተቶች በመሙላት ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ቃል የተገቡ ተግባራትን በትጋት ለመፈጸም በቂ ግንዛቤ የሚፈጠርበት መኾኑን የገለጹት የደብረ ማርቆስ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መልካሙ ሽባባው ናቸው።
በጉባዔው አካታች እና ዲሞክራሲያዊ ብቃት ያለው መሪ ለመፍጠር እና ለመገንባት፣ ተልዕኮዎችን ለማሳካት ዓቅም እንደሚኾን አስገንዝበዋል። በጉባዔው ላይ የተገኙት የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ “የሥራ ኀላፊዎች ራሳቸውን ለመፈተሽ እና ብልሹ አሠራሮችን ለማረም ዝግጁ መኾን አለባቸው” ብለዋል።
ጉባዔው መሪዎች በየዘርፉ የተጣለባቸውን ግዴታ በአግባቡ እንዲወጡ የሚያስችል ስለመኾኑም ገልጸዋል። ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና ጉድለቶችን በመሙላት የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አጋዥ መኾኑን የተናገሩት ተሳታፊ የሥራ ኀላፊዎች በቀጣይ ቃል የተገቡ ተግባራትን ለመፈጸም ቁርጠኛ መኾናቸውን ተናግረዋል።
በደብረ ማርቆስ ከተማ በተካሄደው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛው ቅድመ መደበኛ ጉባዔ የከተማ አሥተዳደር፣ የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ የሥራ ኀላፊዎች ተሳትፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!