“አሚኮ በቴክኖሎጂ እመርታ ጎዳና እየተጓዘ ነው” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)

40

ባሕር ዳር: ጥር 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማ ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ እና የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ ምክትል ሠብሣቢ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አሚኮ የሕዝብ ልሳን እንደኾነ ገልጸዋል፡፡

ዶክተር አሕመዲን ሙሐመድ አሚኮ በቴክኖሎጂ ልቆ የሕዝብ ዐይን እና ጆሮ በመኾን በኢትዮጵያ ብልጽግና እና ሁለንተናዊ ለውጥ ውስጥ በተፈጥሮ እና ሰው ሠራሽ ችግሮች ሳይንበረከክ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እንደሠራም አስረድተዋል።

ዛሬ በይፋ የተመረቀው ኦቢቫን እያደገ በመጣው የሚዲያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ተወዳዳሪ በመኾን ማኅበረሰቡን በማስተማር፣ መረጃን በመስጠት እና በማዝናናት ብሎም ተደራሽ እንዲኾን ትልቅ ፋይዳ አለው ነው ያሉት።

ዓለም የደረሰበትን የሚዲያ ቴክኖሎጂ ማስታጠቅ እና ሙያው በሚፈልገው ክህሎት የሰው ኀይልን ማብቃት እንዲችል የክልሉ መንግሥት ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል፡፡

አሚኮ ሕዝቡ የሚናገርበት እና ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ ኾኖ የሚያገለግልበት እንዲኾን ጥረት እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡ ለአሚኮ ሁለንተናዊ ለውጥ የክልሉ መንግሥት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሰው ተኮር ልማቶች ላይ አተኩሮ መሥራት ተችሏል።
Next articleየደሴ ሙዚየም 90 በመቶ የጥገና ሥራው መጠናቀቁ ተገለጸ።