
ጎንደር: ጥር 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መልእክት የጎንደር ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ ቅድመ መደበኛ ጉባኤ በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው። በጉባኤው ላይ የከተማ፣ የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ መኮንን ፓርቲው የሕዝብ ጥያቄዎችን በመመለስ ሕዝቦች አብረው በጋራ እንዲኖሩ የሚያስችሉ ሥራዎችን እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል። ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ለዚህ አንዱ ማሳያ መኾኑንም አስረድተዋል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ጎንደር ከተማ ለዘመናት የልማት ትኩረት ተነፍጋ መቆየቷን አስታውሰዋል፡፡ ብልጽግና ፓርቲ የከተማዋን ሕዝብ የልማት ጥያቄዎች እየመለሰላት መኾኑንም ተናግረዋል።
በተለይ የኮሪደር ልማት ሥራዎች፣ የመገጭ የውኃ ፕሮጀክት፣ የፋሲል አብያተ መንግሥታት እድሳት እና የአዘዞ ብልኮ የአስፓልት ግንባታ ሥራዎች በፍጥነት እየተሠሩ መኾኑንም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ገልጸዋል።
ዘጋቢ:-ተስፋየ አይጠገብ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!