የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ሰላምን፣ አንድነትን እና አብሮነትን ማስተማር አለባቸው።

16

ደብረ ብርሃን: ጥር 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ባሕላችን እና ኪነ ጥበባችን ለሰላማችን” በሚል መሪ መልዕክት በሰሜን ሸዋ ዞን ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ አዘጋጅነት የባሕል እና የኪነ ጥበብ ዓውደ ርዕይ በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው። የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ መካሻ አለማየሁ የዞኑ ሕዝብ ለዘመናት የመከባበር እና የመዋደድ ባሕል ያለው አብሮነትን ለዘመናት ያቆየ ድንቅ ሕዝብ ነው ብለዋል።

የሃይማኖት አባት እና የሀገር ሽማግሌ የማይከበርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ያሉት አቶ መካሻ የባሕል እና የኪነ ጥበብ ዓውደ ርዕይ መዘጋጀቱ የሕዝቡን የሥልጣኔ መሠረት የኾነ ወግ እና እሴት ይበልጥ እንዲጠናከር ያስችላል ነዉ ያሉት። ዞኑ ከሌሎች ክልሎች እና ብሔረሰብ አሥተዳደሮች ጋር የሚዋሰን በመኾኑ አብሮነትን ይበልጥ የሚያጠናክር የባሕል ግንባታ መገንባት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

“የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ባገኟቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ሰላምን፣ አንድነትን እና አብሮነትን ማስተማር አለባቸው ብለዋል” ዋና አሥተዳዳሪው። የሁነቱ መዘጋጀት የሕዝቡ መገለጫ የኾነውን ነባር እሴት ወደ ነበረበት ለመመለስ መኾኑን የገለጹት ደግሞ የዞኑ ባሕል እና ቱሪዝም መምሪያ ኀላፊ ተዋበች ጌታቸው ናቸው።

በመርሐ ግብሩ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸዉ የተለያዩ የኀብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

ዓውደ ርዕዩ ለተከታታይ ሦሥት ቀናት ይካሄዳል ተብሏል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበወሊድ ምክንያት የሚከሰተውን የእናቶች ሞት ለመቀነስ ሁሉም ትብብር ሊያደርግ እንደሚገባ ጤና ሚኒስቴር አሳሰበ።
Next article“የዘንድሮው የልደት በዓል ቱሪዝሙን ወደነበረበት ለመመለስ የተስፋ ብርሃን የቀደደበት ነው” የላሊበላ ከተማ አሥተዳደር