“አሚኮ አዲስና ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ማሰራጫ ስቱዲዮ መጠቀሙ የሚዲያውን የላቀ ከፍታ ለማሳየት እድል ይፈጥርለታል” የአማራ ክልል ምክር ቤት

41

ባሕር ዳር: ጥር 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሚዲያ ለአንድ ሀገር ግንባታ ትልቅ ሚና እንዳለው የገለጹት የአማራ ክልል ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ከፍያለው ማለፉ በተለይም ለሕዝቦች ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሁነቶችን ተደራሽ ጉልህ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል።

ከዚህ አኳያ በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄዱ ሁነቶችን፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ይዘቶችን በመዘገብ እና በወቅቱ ለሕዝብ ተደራሽ በማድረግ እስካሁን አሚኮ የተጫወተው ሚና ቀላል የሚባል አይደለም ብለዋል፡፡ አሚኮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ፣ ብዝኀነትን እየተላበሰ፣ የሁሉንም አካባቢ ቋንቋ፣ ባሕል እና እሴቶችን እያጎለበተ ትክክለኛ የሕዝብ ሚዲያ መኾኑን እያረጋገጠ የመጣ ሚዲያ ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡

አሚኮ በ12 ቋንቋዎች መረጃዎችን በፍጥነት ተደራሽ በማድረግ በክልሉ ብሎም ከክልሉ ውጭ ላሉ አድማጭ ተመልካቾች የሕዝቦችን አንድነት በማጠናከር ሰላም እና ልማት እንዲረጋገጥ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መኾኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም አስተማማኝ ሰላም በክልሉ እንዲመጣ እና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲረጋገጥ የሚዲያው ሚና በጣም ትልቅ ነው፡፡ ከዚህ ላይ አሚኮ አበክሮ መሥራት ይጠበቅበታል ሲሉ አውስተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ሚዲያው እስካሁን የመጣበት እና ወደፊት እየሄደ ያለበት መንገድም ትክከለኛ ነው ያሉት አቶ ከፍያለው አሁን ደግሞ በያዘው አዲስ ተንቀሳቃሽ ማሰራጫ ስቱዲዮ በመጠቀም ይበልጥ ለሕዝብ ቅርብ፣ ተደራሽ እና ጥራቱን የጠበቀ ዝግጅት ለማቅረብ ያግዘዋል ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አሚኮ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚያስተናግዳቸው ዘገባዎች የሕዝቦችን ትስስር የሚያጠናክሩ ናቸው” የደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ሥራ አሥፈጻሚ ዘላለም ገነሞ
Next article“የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ከውድድር ውጭ አድርጎን ቆይቷል” የሆቴሎች ማኅበር