በደቡብ ወሎ ዞን ከ350 በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የቦርከና ተረፎ የመስኖ ፕሮጀክት ተመረቀ።

39

ደሴ: ጥር 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ከ77 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ ወጪ የተገነባው የቦርከና ተረፎ የመስኖ ፕሮጀክት ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ በተገኙበት ተመርቋል።

ፕሮጀክቱ በቃሉ ወረዳ 3 ቀበሌዎችን ያለማል። ከ350 በላይ የሚኾኑ አርሶአደሮችን የመስኖ ተጠቃሚ ያደርጋል። ከ250 ሄክታር በላይ መሬት ማልማት የሚችል መኾኑም ተመላክቷል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን ( ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የገጠር ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር )፣ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሊ መኮንን እንዲሁም ሌሎች የክልል እና የዞን ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ:-ከድር አሊ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚከናወኑ የፓርቲ ሥራዎች አቅጣጫ የሚሰጥበት ጉባኤ እየተካሄደ እንደሚገኝ የወልድያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ ገለጹ፡፡
Next articleበቦርከና ወንዝ የተገነባው ድልድይ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።