
ወልድያ: ጥር 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት የወልድያ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሁለተኛ ቅድመ መደበኛ ጉባኤ ኮንፈረስ ተጀምሯል። ከቀበሌ እስከ ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ መሪዎች የጉባኤው ተሳታፊ ናቸው። የወልድያ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋዬ ገብሬ በፈተናዎች ሁሉ የነበረን አሸናፊነት ለዛሬ እና ለነገ ጉዟችን ስንቅም ትጥቅም ኾኖ አገልግሏል ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ፈተናን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ወደ ድል የሚቀይር በመኾኑ በቅዥት ዓለም ውስጥ በሚኖሩ ዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች ሳይሸነፍ በርካታ ስኬቶችን አስመዝግቧል ነው ያሉት።
የወልድያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራሬ ለአራት ቀናት በሚቆየው ኮፈረንስ መሪዎች ሃሳብ አመንጭ በመኾን የጉባኤው አቅም ሊኾኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።
እስከ ጥር 4/ 2017 ዓ ም በሚቆየው ጉባኤ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ የመልካም አሥተዳደር እና ሌሎችም ሥራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት እንደሚደረግ ነው የጠቆሙት፡፡
ለቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚከናወኑ የፓርቲ ሥራዎች አቅጣጫ የሚሰጥበት ጉባኤ መኾኑንም ነው ያመላከቱት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!