
ደሴ: ጥር 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን መርቀዋል። በኩታ ገጠም የተዘራ የስንዴ ማሣን ጎብኝተዋል።
በርእሰ መሥተዳሩ ከተመረቁ የልማት ፕሮጀክቶች መካከል በPASDIP የበጀት ድጋፍ 347 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ የሚያደርገው እና 250 ሄክታር የሚያለማው የቦርከና ተረፎ የመስኖ ፕሮጀክት ይገኝበታል። የመስኖ ፕሮጀክቱ ከ77 ሚለዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት ከዞኑ መስኖ እና ቆላማ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሌላው በርእሰ መሥተዳደሩ የተመረቀው ፕሮጀክት 50 ሜትር ርዝመት ያለው እና የሶስት ወረዳ ሕዝብ የሚያገናኛው የቦርከና ድልድይ ሲኾን ክልሉ በመደበው 53 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተገነባ የክልሉ መንገድ ቢሮ መረጃ ያሳያል።
ለምረቃ የበቃው ሌላኛው ፕሮጀክት በቃሉ ወረዳ 034 ቀበሌ የሚገኘው የአርሶ አደር ማሠልጠኛ ጣቢያ ነው። የአርሶ አደር ማሠልጠኛው 13 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበትም ተገልጿል።
ዘጋቢ:- ከድር አሊ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!