
ባሕር ዳር: ጥር 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደቡብ ወሎ ዞን የልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ለመመረቅ ኮምቦልቻ ከተማ ገብተዋል፡፡ ርእሰ መሥተዳድሩ በጉብኝታቸው በደቡብ ወሎ ዞን የተሠሩ የልማት ሥራዎችን ይመርቃሉ። የመስኖ ስንዴ ልማት ሥራዎችንም ይመለከታሉ።
በመርሐ ግብሩም ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን( ዶ.ር)፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር ) ተገኝተዋል።
ርእሰ መስተዳድሩ እና የልዑካን ቡድናቸው ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አሊ መኮንን፣ የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ፣ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ መሃመድ አሚን እና ሌሎች የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!