የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተንቀሳቃሽ ስቱዲዮ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ሙሉቀን ሰጥዬ ያነሷቸዋ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

50

ባሕር ዳር: ጥር 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የአሚኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ሙሉቀን ሰጥዬ በንግግራቸው፦

✍️ አሚኮ ከ30 ዓመት በፊት መታተም በጀመረች የበኩር ልጅ በሆነችው የበኩር ጋዜጣ ስራውን የጀመረ የሚዲያ ተቋም ነው፤

✍️ በአማርኛ ጋዜጣ ብቻ የተጀመረው አገልግሎት አሁን ላይ የምልክት ቋንቋን ጨምሮ በ12 ቋንቋዎች የሚሰራ ብዝኅ ልሳን እና ብዝኅ አገልግሎት ሰጨ የኾነ ሚዲያ መኾን ችሏል፡፤

✍️ ዜና ሰርቶ ለኢትዮጵያ ራዲዮ በመስጠት የጀመረውን የራዲዮ ሥራ ልምምድ በማሳደግ በአሁኑ ወቅት በ7 የራዲዮ ጣቢያዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፤

✍️ አብዛኛውን ሕዝብ ማገልገል የሚቻለው በራዲዮ በመኾኑ ወደ ስርጭት የሚገቡ ተጨማሪ ራዲዮ ጣቢያዎች እንዲኖሩትም እየሰራ ነው፡፡

✍️ አጭር በሚባል ጊዜ ገንዳ ውኃ ላይ ተጨማሪ ራዲዮ ጣቢያ በመክፈት ሀገራዊ ጉዳዮቻችንን በጎረቤት ሀገራት ጨምር በራዲዮ እንዲደርሱ ለማድረግ ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡

✍️ በአንድ ቴቪ ጣቢያ ብቻ የሕዝባችን የሚዲያ ፍላጎት መመለስ የማይቻል በመኾኑ በአሁኑ ወቅት ሁለት የቴቪ ጣቢያዎች እንዲኖሩት ተደርጓል፡፡

✍️ በተለይ ድግሞ ገዥ ትርክትን ለማስረጽ ፣ ለኅብረብሔራዊነት እና ሀገራዊ አንድነት አጋዥ ለመኾን በአሚኮ ኅብር ጣቢያችን ከክልላችን ውጭ የሚገኙ ኢትየጵያዊያንን በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡

✍️ አሚኮ በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ሰምሪት በመስጠት ብቻ ሳይኾን በዜናዎቻችን የቀጥታ ሽፋን መስጠት የቻለ፣ አብሮነት የሚል መስኮት በመክፈት አብሮነትን እየሰበከ ያለ የሕዝብ ሚዲያ ነው፡፡

✍️ አሚኮ ለውጥ እንዲመጣ እና የሕዝብ ጥያቄ እንዲመለስ የሕዝብ ድምጽ የኾነ የሚዲያ ተቋም ነው፤

✍️ ከለውጥ በኃላ የተረጋጋ እና ጠንካራ ሀገር እንድትኖረን፣ ሰላም እንዲሰፍን፤ የምጣኔ ሃብት ጉዳዮችን የማስረጽ፤ ክድህነት እንድንወጣ አጋዠ ኾኗል፤

✍️ ንግግርን እና ውይይትን በማበረታታት የሰለጠነ የፖለቲካ ባሕል እንዲጎለብት ከግጭት መለስ የኾነ የሃሳብ ብዝኀነትን የሚያስተናግድ የሕዝብ ሚዲያ የማድረግ ሥራን በእቅድ እየሰራ ይገኛል፡፡

✍️ የድጅታላይዜሽን እና የኢንተርኔት ዘመን የሚዲያ ተቋማት ተለዋዋጭ ሁኔታ እንዲያልፉ እያስገደደ ሲኾን አሚኮ በድጅታል ሚዲያ አማራጮች ሁሉ ቀድሞ ወደ ተግባር በመግባት የሚለማመድ ሚዲያ ነው፤

✍️ አሚኮ ባለቤቱ የኾነው የአማራ ሕዝብ ወረራ በተፈጠረበት ጊዜ በሁሉም ግምባሮች ቀድሞ የደረሰ በጭና፣ በማካድራ እና ሌሎች አካባቢዎች የደረሰበትን ጭፍጨፋ ቀድሞ ለዓለም ያደረሰ ተቋም ነው፤

✍️ አሁንም ባለው ወቅታዊ የሰላም ችግር ለሕዝብ ስላም እና ልማት ሲል ዋጋ ከፋይ የኾነ የሕዝብ ተቋም ነው፤

✍️ በቴሌቪዥን ዘርፍ ከኢትቪ የአየር ስኣት በመከራየት አገልግሎትን መስጠት ከጀመረ 25 ዓመት ሆኖታል፡፡ በራሱ ጣቢያ ውጥ የኾነ የ18 ስዓት ስርጨት የጀመረው የዛሬ 9 ዓመት ጥር 1/2008 ዓ.ም ነበር፡፡

✍️ ሁሉንም አካባቢ በቅርበት ለማገልገል እና ለሀገራዊ አንድነት የሚጠበቅበትን ለመወጣት ከባሕር ዳር፣ ደሴ እና አዲስ አባባ ዜና ያቀርባል፤ በቅርቡም ከተጨማሪ ከተማ የዜና እወጃ ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ ይገኛል፡፡

✍️ በቅርቡ በተጠናቀቀው አዲስ አባባ ስቱዲዮ ከድሞው የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት አጠናቅቋል።

✍️ስትራቴጂካዊ ሥራዎች እየሠራ ለነገው የሚደያ ዓለም የሚዘጋጅ ሁሌም አዲስ እና ተለዋዋጭ የኾነውን የድህረ እውነት የሚደያ ዓለም ውድድር በብቃት ለመወጣት ይተጋል፡፡

✍️ ሚዲያችሁ አሚኮ ሥራ ያስጀመረው ዘመናዊ የተንቀሳቀሳቃሽ ስቱዲዮው በሁሉም የሀገራችን አከባባቢዎች በሁሉም ቋንቋዎች ለምንሰጠው የቀጥታ ስርጭት ሥራችን ብዙ ምዕራፎችን የሚያሻግር ከነበርነበትም ብዙ እጥፍ ያደገ ጥራት ያለው መረጃ ለማድረስ ዋነኛ አቅም ኾኖ ያገለግላል፡፡

✍️ ባለቤቱ የአማራ ክልል መንግስት እና ሕዝብ ይሁን እንጂ የሚያገለግለው መላ ኢትየጵያዊንን ነው፡፡ ከአራቱም ማዕዘን መረጃዎችን እንሰበስባለን አደራጅተን ለሕዝባችን እናደርሳለን፡፡

✍️ አሚኮ በቀጥታ ስርጭት ሥራ በጉልህ ከሚነሱ እና ብቃቱም ልምዱም ካላቸው ውስን የሚደያ ተቋማት አንዱ ነው፤

✍️ በችግር ወቅትም ቢኾን የሕዝባችን መገለጫ የኾኑ በዓላትን ሳያቆራርጥ የቀጥታ ስርጭት የሚሸፍን በመኾኑ ከበዓላቱ ጎንለጎን አሚኮ የሚወሳባቸው ኾነው ይጠቀሳሉ፡፡

✍️ በዘገባዎቹ ብዙሃን የሚናገሩባቸው እና ለብዙሃን የሚበጁ ጉዳዮች ላይ በትኩረት የሚሰራ ሚዲያ ነው፤ ልሂቃን ብቻ ሳይሆን ብዙሃን የሚናገሩበት፣ የሚጽፉበት እና የሚደመጡበት መሆኑም ልዩ መለያው ነው፡፡

✍️ ለዓመታት አብረውን የዘለቁ ዝግጅቶች በአዲስ መልክ እየተሻሻሉ ጊዜውን የዋጁ ኘሮግራሞች በሁሉም ጣቢያዎች እና ቋንቋዎች ይዞ ለመቅረብ ዘርፈ ብዙ የመሻሻያ ስራዎች ውስጥ ላይ እንገኛለን፡፡

✍️ በቀጣይ የባለቤቱ ሕዝብ የሚዲያ ፍላጎቱ ፈጣን፣ ተለዋወጭ እንዲሁም አዳጊ በመኾኑ የባለቤቱን ልክ የሚመጥን ለሀገር ግንባታ ደርዝ ያለው እና የማይደበዝዝ አሻራ የሚያሳርፍ የሚዲያ ተቋም የማድረግ ሥራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይኾናሉ፡፡

✍️ ሕዝባችንን በቅርበት ለማገልገል የጀመርናቸው ስራዎች በአጭር ጊዜ ወደ ሥራ እንዲገቡ እናደርጋለን፡፡

✍️ ትውልድ ቀረጻ ላይ በመሥራት የነገይቱን ሀገራችን ላይ አሻራ እንዲኖረው የልጆች ቻናል ለመክፈት መሥራት እና ሌሎች ሲተገበሩ የሚታዩ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡

✍️ ግዙፍ የአፍሪካ የሚዲያ ተቋም አድርገን ለማስረከብ ርዐይ አስቀምጥናል፡፡ ለዚህም የሚሆን መሰረት መጣል ጀምረናል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አሚኮ ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስከብሩ ዘገባዎችን እየሠራ ነው“ የአሚኮ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ሙሉቀን ሰጥዬ
Next articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ ገቡ።