
ባሕር ዳር: ጥር 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ተንቀሳቃሽ ስትዲዮው በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የክልሉን ገጽታ የሚገነቡ የቀጥታ ሥርጭቶችን በጥራት እና በፍጥነት ለማሠራጨት የሚያስችል ነው፡፡ በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የብሮድካስት ኢንጂነሪንግ ዳይሬክተር ማንያዘዋል ተሰማ ተንቀሳቃሽ ስትዲዮው ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስምንት ካሜራዎች እንዳሉት ገልጸዋል፡፡
ተንቀሳቃሽ ስቱዲው በክልሉ ስፖታዊ ውድድሮችን በቀጥታ ለማስተላለፍ ትልቅ እገዛ ይኖረዋል፡፡ ስሎው ሞሽን እና መልሶ ማየት የሚያስችል ቴክኖሎጂም ስላለው በተለይም እንደ እግር ኳስ ላሉ ስፖርታዊ ውድድሮችን ለማሰራጨት ጠቀሜታው ጉልህ ነው፡፡
የስፖርት ስታድየሞቻችን ደረጃቸውን የጠበቁ በማድረግ ክልሉ በስፖታዊ ውድድሮች ተመራጭ እንዲኾን ያደርገዋል፡፡ ተንቀሳቃሽ ስትዲዮውን ወደ ተለያዩ ቦታዎች ወስዶ መጠቀም ማስቻሉ እና የውስጥ ቁሳቁሶቹ የዘመኑን ቴክኖሎጂ የያዙ መኾናቸው እንዲሁም ለባለሙያ ምቹ እና ቀላል መኾናቸውን አቶ ማንያዘዋል ገልጸዋል፡፡
ተንቀሳቃሽ ስትዲዮው (ኦቢቫኑ) የራሱ ብቻ የኤሌክትሪክ ኀይል አቅርቦት ያለው ስለኾነ የመብራት ኀይል በሌለባቸውም ቦታዎች እና ጊዜም መሥራት የሚያስችል ነው፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!