
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ጉባዔ ነገ ይካሄዳል።
ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሂደው መደበኛ ጉባዔ ላይ የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚቀርበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ከምክር ቤቱ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!