
አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአዊ ብሔረሰብ ተወላጆች የገና ጨዋታ አካሂደዋል።
ከገና ጨዋታው በተጨማሪ በገና ባሕላዊ ጨዋታዎች እና ጭፈራዎች ባሕሉን በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል።
ዝግጅቱን በምርቃት ያስጀመሩት የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሸማግሌዎች በየዓመቱ የሚካሄደው የአገው ባሕላዊ የገና ጨዋታ የማኅበረሰቡን ባሕላዊ እና ሃይማኖታዊ ትውፊቶች የማስቀጠል ዓላማ ያለው መኾኑን አንስተዋል።
ወጣቱ ትውልድ የብሔረሰቡን ባሕል እና ወግ አስጠብቆ በማስቀጠል በኩል ትልቅ ኀላፊነት እንዳለበትም የሃይማኖት አባቶች ተናግረዋል።
የአገው ባሕላዊ የገና ጨዋታ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ለባለፉት 15 ዓመታት በአዲስ አበባ እየተተገበረ እንደሚገኝም ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!