የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ የልደት በዓልን ለማክበር ላሊበላ ገቡ።

86

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ የልደት በዓልን ለማክበር ላሊበላ ገብተዋል።

ሚኒስትሯ ላሊበላ ሲደርሱ የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ መልካሙ ጸጋዬ፣ የላሊበላ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ወንድምነው ወዳጅን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በላሊበላ በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ይከበራል። በዓሉ ከሃይማኖታዊ ሥርዓት ባለፈ ታላቅ የቱሪዝም መዳረሻ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየልደት በዓል የገበያ በባሕር ዳር
Next articleሰው ፍቅር እና ይቅርታን ከክርስቶስ መማር አለበት።