
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 28:2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ የልደት በዓልን ለማክበር ላሊበላ ገብተዋል። የሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎችም የልደት በዓልን ለማክበር ላሊበላ ገብተዋል።
አፈ ጉባኤዋ ላሊበላ ሲደርሱ የላሊበላ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ወንድምነው ወዳጅ እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትም የልደት በዓልን ለማክበር ላሊበላ እየገቡ ነው። የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በላሊበላ ከዋዜማው ጀምሮ በድምቀት ይከበራል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!