“በጉምቱ ፖለቲከኛ ህልፈት ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶኛል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

48

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የአቶ ቡልቻ ደመቅሳን ህልፈት ተከትሎ የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የተከበሩ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሰላማዊ ትግል ውስጥ ትልቅ አስተዋፅዖ አበርክተዋል ብለዋል።

አቶ ቡልቻ ለሀገር ሁለንተናዊ ጥቅም የሰሩ እና ለችግሮችም እራሳቸውን የመፍትሔ አካል አድርገው ጽናትን ያሳዩ ሰው ነበሩ ብለዋቸዋል፡፡ “በጉምቱ ፖለቲከኛ ህልፈት ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶኛል”ም ብለዋል፡፡

ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር።

ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመድና ኢትዮጵያዊያን መጽናናትን እመኛለሁ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፍ።
Next articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት !