“አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በማረፋቸው የተሰማኝን ሃዘን እገልጻለሁ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

49

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የአቶ ቡልቻ ደመቅሳን ህልፈት አስመልክተው የሃዘን መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀዘን መግለጫቸው አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በሚችሉት ሁሉ ሀገራቸውንና አፍሪካን ያገለገሉ፣ በአቋማቸው ጽኑ፣ ሕዝቦችን ለማቀራረብ የተጉ፣ እውነት ነው ብለው ያመኑትን የትም እና መቼም የሚናገሩ ነበሩ ብለዋቸዋል።

እንዲህ ዓይነት ብርቱ ሽማግሌዎችን ማጣት ጉዳቱ ለሀገር ነው። ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይቀበላት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleወደ ልመና የወጣው አባት?
Next articleየልደት በዓል የተጣሉ ፍጥረታት የታረቁበት ዕለት ነው።