ወቅታዊ መረጃ !

58

በአፋር፤ ኦሮሚያ እና አማራ ከልል አዋሳኝ አካባቢዎች ማዕከላቸውን አድርገው የተለያየ መጠን ያላቸው የርዕደ መሬት ክሥተቶች በተደጋጋሚ መከሠታቸው ይታወቃል።

ክሥተቶቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጠን እና በድግግሞሽ እያደጉ ይገኛሉ። በተለይም በዚህ ሳምንት በርዕደ መሬት መለኪያ እስከ 5.8 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ መንቀጥቀጥ መከሠቱን መረጃዎች ያሳያሉ።

መንግሥት ክሥተቶቹን በዘርፉ ባለሞያዎች በቅርብ እየተከታተለ ይገኛል። በተጨማሪም በተለይ የርዕደ መሬቱ ማዕከል (epicenter) የሆኑት አካባቢዎችን በመለየት በ12 ቀበሌዎች ላይ መንግሥት ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተውጣጡ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በቦታው በማሰማራት የጉዳቱን መጠን አሠሣ እያደረገ ይገኛል። በእነዚህ ቀበሌዎች ከሚኖሩ 80 ሺህ ዜጎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን በመለየት ነዋሪዎችን ከአካባቢው በማራቅ ለማሥፈር ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ነው።

በተጨማሪም ርዕደቱ በማኅበራዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት፤ በኢኮኖሚ ተቋማት እና በመሠረተ ልማት ላይ ሊኖረው የሚችሰውን ተጽዕኖ በመከታተል ላይ ነው።

እስካሁን ባለው ሁኔታ በዋና ዋና ከተሞች የጎላ ተጽዕኖ ያላደረሰ ቢሆንም ዜጎች በባለሞያዎች የሚሰጡ የጥንቃቄ መልእከቶችን እንዲከታተሉና በጥብቅ አንዲተገብሩ ለማሳሰብ እንወዳለን።

በቀጣይም ጉዳዩን በቅርበት በመከታተል አስፈላጊ መረጃዎችን በሚመስከታቸው ተቋማት አማካይነት የሚያደርስ መሆኑን መንግሥት ያስታውቃል።

በኢፌዲሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ታኅሣሥ 26 ቀን 2017 ዓ.ም

Previous articleኢትዮ ቴሌኮም የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ለማሳካት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገለጸ።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በጅግጅጋ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ጎበኙ።