
የግል መገናኛ ብዙኃን ለሀገርና ለትውልድ ግንባታ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በሀገራችን ፋና ወጊ ከሆኑ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀዳሚነት የሚጠቀሰውን የኢቢኤስን የቴሌቪዥን ጣቢያ ጎብኝተናል፡፡
ኢቢኤስ ባለፉት 15 ዓመታት በግሉ የሚዲያ ዘርፍ በርካታ የመዝናኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለሕዝብ በማድረስ ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ በተጨማሪም ተቋሙ የኢትዮጵያን ውብ ባሕል፣ ታሪክና ማኅበራዊ መስተጋብር አጉልቶ ለዓለም ተደራሽ እያደረገ መሆኑ ይበል ያሰኛል።
የጠፉ ቤተሰቦችን በማገናኘት እና ለተቸገሩ ወገኖች ብሩህ ተስፋ በመሆን የጀመረው ሥራም ለሌሎች መገናኛ ብዙኃን አርአያ የሚሆን ነው።
የሚዲያ ተቋሙ የሀገራችንን የጥበብ መናገሻነት የሚያሳዩ ታሪካዊ፣ ትምህርት ሰጭና አዝናኝ ፕሮግራሞችን በማሳየት ለኪነ ጥበብ ዕድገት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽዖ አጠናክሮ መቀጠል አለበት።
የግል መገናኛ ብዙኃን ዐቅማቸውን አሳድገው በዘርፉ ተወዳዳሪ ለመሆን፤ አስተማሪ እና ትውልድን የሚያንፁ ፕሮግራሞችን መሥራት ይጠብቅባቸዋል፡፡ መንግሥትም ለግል መገናኛ ብዙኃን መጠናከር ምቹ ምኅዳር ከመፍጠር ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!