
ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሴቶች ማኅበር ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸሙን በባሕር ዳር ከተማ እየገመገመ ነው። የአማራ ሴቶች ማኅበር ዳይሬክተር ገነት ወንድም እንዳሉት ማኅበሩ የተዛባ የሥርዓተ ፆታ አስተሳሰብ እና ተግባርን ለማስወገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ሴቶች በክልላቸው በምጣኔ ሃብት፣ በማኅበራዊ፣ በመልካም አሥተዳደር እና በፖለቲካ ተሳትፏቸው እያደገ እንዲመጣ ዓይነተኛ ሚና ተጫውቷልም ብለዋል። ዳይሬክተሯ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በሥነ ልቦና የማከም እና በኢኮኖሚ የማቋቋም ሥራዎች ስለመከናወናቸውም ነው የገለጹት።
በማኅበራዊ ልማት ተሳትፎም ላቅ ያለ ሥራ እንደተሠራ አስገንዝበዋል።
በተዛባ ትርክት ሰፍኖ የቆየውን የሴቶች የንብረት ባለቤትነት መብት እንዲረጋገጥም ተደርጓል ብለዋል ዳይሬክተሯ። የማኅበሩ የቦርድ ጸሐፊ ማኅሌት ጥላሁን የተጎዱ እና ችግር የደረሰባቸው ሴቶች አንገታቸውን ደፍተው እንዳይቀሩ ማኅበሩ አድርጓልም ብለዋል።

በተባበሩት መንግሥታት የሥነ ሕዝብ ፈንድ የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለሙያ አዳነች ሽፈራው በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መከላከል እና ምላሽ መስጠት ለአንድ አካል ብቻ የሚሰጥ እንዳልኾነም አስረድተዋል።
ችግሩን ለመፍታት የሁሉንም ዙሪያ መለስ ርብርብ፣ እገዛ እና ድጋፍ ይሻልም ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
