የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለክልሎች የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

34

አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከወርልድ ባንክ በተገኘ 1 ቢሊዮን ብር ወጭ የተገዙ የሞተር ሳይክሎች እና የላብራቶሪ መሣሪያዎችን ነው ድጋፍ ያደረገው።

የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሃይሉ የጤና ሥርዓቱ የተሳለጠ እንዲኾን ኢንስቲትዩቱ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተለይ የዲጂታል አገልግሎት ሥርዓቱ ጊዜውን የጠበቀ፣ አስተማማኝ የኅብረተሰብ ጤና መረጃ አያያዝ የተሻለ እንዲኾን እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል። የጤና ተቋማትን በሕክምና መሣሪያ፣ በመድኃኒት እና ሌሎች ቁሳቁሶች በማደራጀት በተለይም የእናቶችን እና ህጻናትን ሞት ለመቀነስ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ከወርልድ ባንክ በተገኘ 7 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዶላር የተገዙ የሕክምና ቁሳቁሶች ለክልሎች ድጋፍ መደረጉን አንስተዋል። የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የተደረገው ድጋፍ ክልሎችን የጤና አደጋዎችን ቀድሞ ለመከላከል ያስቻላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከተለያዩ ለጋሽ አካላት ጋር በጤናው ዘርፍ በርካታ አመርቂ ሥራዎችን እየሠራ መኾኑን የተናገሩት ሚኒስትሯ ክልሎች ያገኙትን ድጋፍ ተጠቅመው ለኅብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስበዋል።

ለተደረገው ድጋፍም ሚኒስትሯ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዘጋቢ:- ሰለሞን አሰፌ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የነዳጅ አቅርቦትን እና የወደብ አገልግሎትን ማሳደግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ተስማሙ።
Next article“ፓርቲው ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የገባውን ቃል ከስኬት ለማድረስ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል” ከንቲባ አዳነች አቤቤ