ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የነዳጅ አቅርቦትን እና የወደብ አገልግሎትን ማሳደግ በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ተስማሙ።

38

አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ.ር) በጅቡቲ ያደረጉት ጉብኝት ስኬታማ እንደነበር ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ በሀገሪቱ በነበራቸው ቆይታ ከፕሬዚዳንት ዑመር ጌሌህ ጋር በሁለቱ ሀገራት እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል ነው ያሉት።

በመንገድ ግንባታ፣ የነዳጅ አቅርቦትን በማፋጠን፣ አልሻባብን ለመዋጋት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ እና የወደብ አገልግሎትን ማስፋት በሚቻልበት ዙሪያ ስምምነት ላይ ስለመደረሱ አንስተዋል።

በሌላ በኩል 38ኛው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤን በአግባቡ ለማስተናገድ በቂ ዝግጅት ስለመደረጉም አስገንዝበዋል። በጉባኤው ኢትዮጵያን የሚጠቅሙ አጃንዳዎች አንዲንሸራሸሩ ለማድረግ በቂ ዝግጅት ተደርጓልም ነው ያሉት።

ቃል አቀባዩ ሁሉም ዜጋ ዲፕሎማት ነው በሚለው መርሕ መሠረት አረበኛ፣ ፈረንሳይኛ እና እንግሊዘኛ የሚችሉ ወጣቶች በበጎ ፍቃድ እንዲሰማሩ ለማድረግ ዝግጅት ስለመደረጉም አስገንዝበዋል።

በሱዳን ሰላም እንዲመጣ ኢትዮጵያ ድጋፍ ታደርጋለችም ብለዋል። ከሶማሊያ ጋርም ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እየሠሩ ስለመኾኑ ቃል አቀባዩ አስረድተዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ የተመራ ልዑክም በሞቃዲሾ ውይይቶች ማድረጉንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ተናግረዋል።

ዘጋቢ፦ አንዱዓለም መናን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየወባ ሥርጭት አሳሳቢነት
Next articleየኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለክልሎች የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።