
ባሕር ዳር: ታኅሳስ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ)ብሪክስ ዘጠኝ ሀገራትን በአጋርነት መቀበሉ ታውቋል፡፡ ጥምረቱ በአጋርነት የተቀበላቸው ሀገራትም ቤላሩስ፣ ቦሊቪያ፣ ኩባ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ካዛኪስታን፣ ማሌዥያ፣ ታይላንድ፣ ኡጋንዳ እና ኡዝቤኪስታን ናቸው፡፡
ጥቅምት ወር 2024 በሩሲያ ካዛን በተካሄደው የብሪክስ ጉባኤ ላይ 13 ሀገራት ጥምረቱን በአጋርነት እንዲቀላቀሉ ግብዣ ቀርቦላቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ በሩሲያ፣ ቻይና፣ ሕንድ እና ብራዚል የተመሠረተው ብሪክስ ፤ ደቡብ አፍሪካን በ2010፣ ኢትዮጵያን፣ ኢራንን፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን እና ግብጽን ደግሞ በ2024 በአባልነት መቀበሉ ይታወቃል፡፡
እንደ ቻይና እና ሩሲያ ያሉ የዓለም ኃያላን ሀገራትን ያቀፈው ብሪክስ ከ3 ነጥብ5 ቢሊዮን የሚበልጥ ሕዝብን እንደሚወክል ዘ ሳውዝ አፍሪካን ዶት ኮም ዘግቧል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!