“በአማራ ክልል ሰላምን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች አበረታች ናቸው” ሚኒስትር ድኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ

14

ባሕር ዳር: ታኅሳስ 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ የተመራ ልዑክ በደሴ ከተማ፣ በደቡብ ወሎ ዞን፣ በኮምቦልቻ ከተማ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የልማት ተግባራትን ተመልክቷል። በደሴ ከተማ የልማት ሥራዎችን በአጭር ጊዜ እና በጥራት ጀምሮ በማጠናቀቅ ረገድ ለሌሎች ከተሞች ተሞክሮ ለመኾን የሚያስችል ተግባር መመልከታቸውን ሚንስትር ዴኤታው ገልጸዋል።

በኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደርም እየተተገበሩ ያሉ ሰው ተኮር ተግባራት የተማሪዎች ምገባ፣ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት ግንባታ እና የኮሪደር ልማቱ የዜጎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ሥራዎች መኾናቸውን ነው ሚንስትር ዴኤታው ያብራሩት። በደቡብ ወሎ ዞን እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደርም ሰላምን በማስፈን እና የልማት ሥራዎችን በመፈጸም ረገድ አበረታች እና የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት መከናወናቸውን ተመልክተናል ብለዋል።

በአማራ ክልል ለልማት የተሰጠው ትኩረት እና የተገኙ ውጤቶች አበረታች መኾናቸውን ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል። ማኅበረሰቡ የልማት ተግባራቱን በባለቤትነት ስሜት እያከናወነ እንደሚገኝ ተገንዝበናል ብለዋል።

የተጀመሩ የልማት ሥራዎችም ከዳር ለማድረስ ማኅበረሰቡ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታው ተስፋሁን ጎበዛይ አሳስበዋል።

ዘጋቢ:- አንተነህ ፀጋዬ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ መልእክት!
Next articleእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግ በትኩረት እየሠራን ነው።