
ኢቢሲ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ ባህልና ማኅበራዊ እሴቶች በማስተዋወቅ እና ለመልካም ገፅታ ግንባታ እያደረገ ያለው ጥረት ለሌሎች መገናኛ ብዙኃን ምሳሌ መሆን የሚችል ነው፡፡ ዛሬ ሸጎሌ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና መሥሪያ ቤት ጎብኝተናል፡፡
ተቋሙ ዘመኑን የዋጀ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ከመገንባት ባሻገር “ወደ ይዘት” በሚል መሪ ቃል በጀመረው የይዘትና የአቀራረብ ማሻሻያ ተደራሽነቱን ለማስፋት እየሠራቸው የሚገኙ ተግባራት አበረታች ናቸው፡፡
ኢቢሲ በተለያዩ ክልሎች አዳዲስ ስቱዲዮዎችን ገንብቶ ወደ ሥራ ማስገባቱ የኢትዮጵያን አዎንታዊ መልክ ለማጉላትና የወል ትርክትን ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖረዋል፡፡
ተቋሙ ተአማኒና ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ለመሆን፣ የሀገርን ታሪክና ባሕል ለማስከበር እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲፈጠር፤ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል፡፡
ኢቢሲ አሁን ካለው ደረጃ ወደ ተሻለ ምእራፍ እንዲሸጋገር መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡