“የአዕምሯዊ ንብረት ምንነትን እና ፋይዳን ለኅብረተሰቡ በማስረጽ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል” የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን

35

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ከኢፌዴሪ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ጋር በመተባበር “የንግድ ምልክት ምንነት እና አስፈላጊነት እንዲሁም የምዝገባ ጠቀሜታ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማሳደጊያ ሥልጠና” በባሕር ዳር ከተማ እየተሰጡ ነው።

በኢትዮጵያ የአዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ኀላፊ ናስር ኑሩ እንዳሉት የአእምሯዊ ንብረት ምንነትን በኅብረተሰቡ ዘንድ በማስረጽ በሃብቱ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል።

ዓለምን እየመራ ያለው የአዕምሯዊ ንብረት ነው ያሉት አቶ ናሥር ኑሩ ኅብረተሰቡ ስለ አዕምሯዊ ንብረት በውል ተገንዝቦ ሀገሪቱ እየተገበረች ባለው የቴክኖሎጂ ሽግግር የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጣ ያስችለዋል።

ለዚህ ደግሞ ባለድርሻ አካላት በጉዳዩ ዙሪያ ግንዛቤያቸውን በማሳደግ ወደ ኅብረተሰቡ ማስፋፋት ተገቢ ነው ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለክልሉ አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለመስጠት ይሠራል።
Next article“ኑ ድንቁን ነገር ተመልከቱ፣ የበረከት ተካፋይም ሁኑ” አባ ሕርያቆስ ጸጋዬ