ለክልሉ አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለመስጠት ይሠራል።

42

ደሴ: ታኅሣሥ 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ወሎ ዞን መሬት መምሪያ የአምስት ወራት የዘመናዊ መሬት አሥተዳደር ሥርዓት (ካዳስተር) ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በደሴ ከተማ አካሂዷል። በግምገማ መድረኩ የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ምክትል ኀላፊ እብሬ ከበደ፣ በዞኑ የሚገኙ የ23ቱም የወረዳ እና ከተማ አሥተዳደር መሬት ጽሕፈት ቤት ኀላፊዎች እና የቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል።

ለአርሶ አደሩ የሁለተኛ ደረጃ የይዞታ ማረጋገጫ በመሰጠቱ ባለፉት አምስት ወራት ከ500 ሺህ ብር በላይ ገቢ መሠብሠብ መቻሉን የተንታ ወረዳ መሬት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አረጋ ጥላሁን ገልጸዋል። የቃሉ ወረዳ መሬት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ፈንታው ሽፈራው በወረዳው ላሉ ወጣቶች 32 ሄክታር መሬት ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በማስተላለፍ የተለያዩ የግብርና ሥራዎችን እንዲያከናውኑበት መሰጠቱን ተናግረዋል።

በሁለተኛ ሩብ ዓምት ለ135ሺህ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ባለፉት አምስት ወራት ተሰጥቷል ያሉት የደቡብ ወሎ ዞን መሬት መምሪያ ኀላፊ አብዱሮህማን ይመር ለአርሶ አደሩ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መተላለፉን ገልጸዋል። የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ምክትል ኀላፊ እብሬ ከበደ በክልሉ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በመስጠት የብድር ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።

በቀጥይ ወራትም ለክልሉ አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ለመስጠት እንደሚሠራም ነው ያስገነዘቡት።

ዘጋቢ፦ሰለሀዲን ሰይድ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article‘ጥርን በባሕር ዳር፤ ባዛራችን ለሰላም” የንግድ አውደ ርዕይ እና ባዛር ሊካሄድ ነው።
Next article“የአዕምሯዊ ንብረት ምንነትን እና ፋይዳን ለኅብረተሰቡ በማስረጽ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል” የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን